Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወንድሞቼ ሆይ! በሌሎች አሕዛብ መካከል ብዙ አማኞችን እንዳገኘሁ እንዲሁም በእናንተ መካከል አማኞችን ለማግኘት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ወደ እናንተ ለመምጣት ብዙ ጊዜ ዐቅጄ እስከ አሁን ያልተሳካልኝ መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ወንድሞች ሆይ፤ በሌሎች አሕዛብ ዘንድ እንደ ሆነልኝ፣ በእናንተም ዘንድ ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ ዐቅጄ ሳለሁ፣ እስከ አሁን ድረስ ግን መከልከሌን እንድታውቁ እወድዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 1:13
38 Referencias Cruzadas  

በሚመጡት ዘመናት የያዕቆብ ዘር የሆኑ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ወይን ግንድ ሥር ይሰዳሉ፤ አብበውም ያፈራሉ፤ ፍሬአቸውም ምድርን ይሞላል።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በመሬት ወድቃ ካልሞተች፥ ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ታፈራለች።


እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።


የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘለዓለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፥ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መቶ ኻያ በሚያኽሉ አማኞች መካከል ቆመና እንዲህ አለ፦


እዚያም በደረሱ ጊዜ አማኞችን በአንድነት ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉና አሕዛብም እንዲያምኑ እንዴት አድርጎ በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።


በዚህ ጊዜ ጉባኤው ጸጥ ብሎ በርናባስና ጳውሎስ በእነርሱ አማካይነት እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ተአምርና ድንቅ ነገር ሁሉ ሲናገሩ በመገረም አዳመጣቸው።


ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።


ጳውሎስ ለሁሉም ሰላምታ ከሰጠ በኋላ በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ሁሉ አንድ በአንድ ተረከላቸው።


እዚያ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሮም ሄድን።


ይህንንም ማለቴ እኔ በእናንተ እምነት፥ እናንተም በእኔ እምነት እርስ በእርሳችን እንድንጽናና ነው።


ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።


ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አታውቁምን? የምናገረው ሕግን ለሚያውቁ ሰዎች ነው፤ ሕግ በሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ ነው።


ወንድሞቼ ሆይ! “መለያየት በመካከላችሁ አይኑር፤ ሁላችሁም ተስማምታችሁ በአንድ ሐሳብና በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ ኑሩ” ብዬ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።


ወንድሞቼ ሆይ! አባቶቻችን ደመና ከበላያቸው ሆኖ ይመራቸው እንደ ነበረና ሁሉም ቀይ ባሕርን እንደ ተሻገሩ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።


ወንድሞቼ ሆይ! አሁን ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንድታውቁ እፈልጋለሁ።


ወንድሞቼ ሆይ! ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁስ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ይልቁንም በአስተሳሰባችሁ የበሰላችሁ ሁኑ።


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።


በጌታ የሐዋርያነቴ ማረጋገጫ ማኅተም እናንተ ስለ ሆናችሁ ለሌሎቹ እንኳ ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተ ግን በእርግጥ ሐዋርያ ነኝ።


ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር።


ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን!


ወንድሞቼ ሆይ! እስቲ ይህን ነገር በሰው ዘንድ ከተለመደ ነገር ጋር አነጻጽሩት፤ አንድ ሰው የገባው ቃል ኪዳን እንኳ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሰው ሊሽረው ወይም ሊጨምርበት አይችልም።


ወንድሞች ሆይ! የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን! አሜን።


ይሁን እንጂ በዚሁ ሥጋዊ አካሌ ቀጥዬ የምኖር ብሆን ፍሬ የሚሰጥ ሥራ መሥራት ማለት ነው፤ ሆኖም ግን ቀጥዬ ከመኖርና ከመሞት የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።


ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኘት በመጓጓት ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።


እንዲሁም ለጌታ ተገቢ በሆነ መንገድ በመኖር እርሱን በፍጹም እንድታስደስቱ ማናቸውንም መልካም ሥራ በመሥራት ፍሬ እንድታፈሩና እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ እንድትሄዱ እንጸልያለን።


እናንተ ወንጌልን ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርንም ጸጋ እውነተኛነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ ይህ ወንጌል በእናንተ መካከል እንደሆነው በመላው ዓለም በማፍራትና በማደግ ላይ ነው።


ወደ እናንተ መምጣት ፈልገን ነበር፤ በተለይም እኔ ጳውሎስ ወደ እናንተ ለመምጣት ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ከለከለን።


ወንድሞች ሆይ! ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ስለ ሞቱት ሰዎች እውነቱን እንድታውቁ እንወዳለን።


ምሥጢራዊው የዐመፅ ኀይል አሁንም በመሥራት ላይ ነው፤ ሆኖም አሁን የሚከለከለው አለ፤ ይህም የሚሆነው ያ የሚከለክለው እስኪወገድ ድረስ ነው።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos