ኢዮአብም “አንተ ይህን ቃል ባትናገር ኖሮ የእኔ ሰዎች እስከ ነገ ጠዋት ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንደማይገቱ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” ሲል መለሰለት።
ኢዮብ 27:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ትክክለኛ ፍርድ በመከልከል፥ ሕይወቴን እጅግ መራራ ባደረገው ሁሉን በሚችል በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደዚህ የፈረደብኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን! |
ኢዮአብም “አንተ ይህን ቃል ባትናገር ኖሮ የእኔ ሰዎች እስከ ነገ ጠዋት ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንደማይገቱ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ” ሲል መለሰለት።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።
የያዕቆብ ዘር የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! “አካሄዴ ከእግዚአብሔር የተሰወረ ነው፤ መብቴም በእርሱ ዘንድ ችላ ተብሎብኛል፤” ብለህ ለምን ታማርራለህ?
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።
እስኪነጋ እዚሁ ቈዪ! ሲነጋም ያ ሰው ስለ አንቺ ኀላፊነትን የሚወስድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እጠይቀዋለሁ፤ እርሱ ኀላፊነትን የሚወስድ ከሆነ መልካም ነው፤ የማይወስድ ከሆነ ግን ስለ አንቺ ኀላፊነትን እኔ እንደምወስድ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አሁንም ተኚ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ቈዪ።”
በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን “ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል ያስገኘ ዮናታን ይሞታልን? ከቶ አይደረግም! መሞቱ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም እንምላለን፤ ዛሬ እርሱ ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ረዳትነት የተፈጸመ ነው” አሉ፤ በዚህም ዐይነት ሕዝቡ ዮናታንን ከሞት ቅጣት አዳኑት።
ከዚያም በኋላ ፍላጻዎቹን እንዲያመጣ ልጁን እልካለሁ፤ ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወደዚህ ናቸውና አምጣቸው!’ ካልሁት አንተ ከተደበቅኽበት ቦታ ልትወጣ ትችላለህ፤ ስለዚህ ምንም ችግር እንደማይደርስብህና ምንም አደጋ እንደሌለ በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤
በአንቺ ላይ ጒዳት ከማድረስ እግዚአብሔር ጠብቆኛል፤ ፈጥነሽ ወደ እኔ ባትመጪ ኖሮ ግን፥ ከናባል ወንዶች አንድ እንኳ ሳላስተርፍ ከንጋት በፊት ሁሉንም ለመግደል በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ነበር።”