ኤርምያስ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ በዚህ ሁሉ ነገር እነርሱን ልቀጣቸውና እንደነዚህ ያሉትንስ ሕዝብ ልበቀላቸው አይገባኝምን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንደዚህ ዐይነቱንስ ሕዝብ፣ አልበቀልምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፋቸውምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ስለዚህ ነገር በመቅሠፍት አልጐበኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን? |
በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?
ከሸለቆ ለስላሳ ድንጋዮች መካከል መርጣችሁ አማልክታችን ናቸው በማለት የመጠጥና የእህል ቊርባን ታቀርቡላቸዋላችሁ። በዚህ ነገር አልቈጣምን?
“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።