Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 9:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ታዲያ ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንደዚህ ዐይነቱንስ ሕዝብ፣ አልበቀልምን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀስፋቸውምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ታዲያ በዚህ ሁሉ ነገር እነርሱን ልቀጣቸውና እንደነዚህ ያሉትንስ ሕዝብ ልበቀላቸው አይገባኝምን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 9:9
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “ወዮ! በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።


በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


በሸለቆው በሚገኙት ለስላሳ ድንጋዮች ውስጥ ያሉት ጣዖቶች የአንቺ ናቸው፤ እነርሱም ዕጣ ፈንታዎችሽ ናቸው፤ ርግጥ ነው፣ በእነርሱ ላይ የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፤ የእህል ቍርባንም አቅርበሻል፤ ታዲያ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዝም እላለሁን?


በፊቴ ባድማ፣ ደረቅና ወና ይሆናል፤ መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና።


ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።


አየሁ፤ ሰው አልነበረም፤ የሰማይ ወፎች ሁሉ በረው ጠፍተዋል።


ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር። “እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣ እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?


ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀጣቸውምን?” ይላል እግዚአብሔር። “እኔ ራሴ እንደዚህ ዐይነቱን ሕዝብ አልበቀልምን?


ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።


አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ያልተነካውን መሰማሪያ እሳት በልቶታልና፤ የዱሩን ዛፍ ሁሉ ነበልባል አቃጥሎታል።


የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤


“ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ በገዛ ምድሯ ተጣለች፤ የሚያነሣትም የለም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos