ኤርምያስ 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ድምፄንም አልሰሙምና፥ በእርሱም አልተመላለሱምና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋል፤ ቃሌንም አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥ |
“ነገር ግን አምላካችን ሆይ! እስከ አሁን ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ምን ማለት እንችላለን? እነሆ፥ አሁንም እንደገና ትእዛዞችህ አላከበርንም፤
እነዚህ በክፋት የተሞሉ ሕዝብ ለእኔ መታዘዝን እምቢ ብለዋል፤ ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞች ሆነዋል፤ ባዕዳን አማልክትን በማምለክ ያገለግላሉ፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ ዋጋቢስ ሆኖ እንደ ቀረው እንደዚያ መታጠቂያ ይሆናሉ።
እናንተ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችሁ ባዕዳን አማልክትን በማምለካችሁና በማገልገላችሁ ምክንያት መሆኑንም ይረዳሉ።”
ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ያደረሰብን ስለምድን ነው?’ ብለው በጠየቁህ ጊዜ ከእኔ ተለይተው በገዛ ምድራቸው ላይ ባዕዳን አማልክትን እንዳመለኩ ሁሉ፥ እነርሱም ራሳቸው የእነርሱ ባልሆነ አገር የባዕድ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸው እንደማይቀር ንገራቸው።”