53 ክፉ ሰዎች ሕግህን ሲተላለፉ በማየቴ በብርቱ ተቈጣሁ።
53 ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ።
53 ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።
ቀጥሎም ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበረው ስፍራ በመነሣት የኤልያሺብ ልጅ ዮሐናን ወደሚኖርባቸው ክፍሎች ገባ፤ ምርኮኞቹ እምነት በማጓደል ስለ ፈጸሙትም በደል ሁሉ እያዘነ ሌሊቱን በዚያው አነጋ፤ እህልም ሆነ ውሃ አልቀመሰም።
ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን?
እኔም ይህን በሰማሁ ጊዜ በሐዘን መጐናጸፊያዬንና ካባዬን ቀደድሁ፤ የራስ ጠጒሬንና ጢሜን በመንጨት በብርቱ ሐዘን ላይ ሆኜ ተቀመጥሁ፤
እነዚህንም ሰዎች ገሠጽኳቸው፤ ረገምኳቸውም፤ ደብድቤም ጠጒራቸውን ነጨሁ፤ ከዚህም በኋላ እነርሱም ሆኑ ልጆቻቸው ከባዕዳን ሕዝብ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ በእግዚአብሔር ስም አስማልኳቸው።
እኔም አቤቱታቸውን በሰማሁ ጊዜ ተቈጣሁ፤
ሰዎች ሕግህን ስለ ጣሱ እንባዬ እንደ ወንዝ ውሃ ይፈስሳል።
ቃልህን ስለማይጠብቁ፥ ከሐዲዎችን አይቼ ተጸየፍኳቸው።
“ነገር ግን የእርሱ ዘሮች ሕጌን ቢጥሱ፥ በሥርዓቴም ባይኖሩ፤
አናዳምጥም ብትሉ ግን ስለ ትዕቢታችሁ ተደብቄ አለቅሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምርኮኞች ሆነው በመወሰዳቸውም ምርር ብዬ አለቅሳለሁ፤ እንባዬም ባለማቋረጥ ይፈስሳል።
በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል እጅግ ከመደንገጡና በሐሳብ ከመታወኩ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ፤ ንጉሡም “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ አያስጨንቅህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ ለአንተ መሆኑ ቀርቶ ለጠላቶችህ ቢሆን በወደድሁ ነበር።
ይህን ሁሉ ስሰማ ሰውነቴ ይርበደበዳል፤ ድምፁም ከንፈሮቼን ያንቀጠቅጣል፤ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼ ከታች ይብረከረካሉ፤ በጠላቶቻችን ላይ መከራ የሚደርስበትን ጊዜ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ አምላኬ ምናልባት በእናንተ ፊት ያዋርደኛል ብዬ እፈራለሁ፤ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ሠርተው በዚሁ በሠሩት ርኲሰት፥ ዝሙትና፥ ስድነት ንስሓ ስላልገቡት ሰዎች ሐዘን ላይ እወድቃለሁ ብዬ እፈራለሁ።
ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ እንደ ነገርኳችሁና አሁንም እንባዬን እያፈሰስኩ እንደምነግራችሁ ሁሉ ብዙዎቹ በአካሄዳቸው የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዋል።