“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ኤርምያስ 7:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተመልከቱ! እናንተ እኮ በሚያታልሉ ከንቱ ቃላት ትተማመናላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ግን፣ ከንቱ በሆኑ የሐሰት ቃላት ታምናችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ በማይረባ በሐሰት ቃላት ታምናችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ በማትጠቀሙበት በሐሰት ቃል ብትተማመኑም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በማትረቡበት በሐሰት ቃል ታምናችኋል። |
“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
እነሆ እኔ እግዚአብሔር የምለውን አድምጡ! በሐሰት የተሞላ ሕልማቸውን የሚናገሩ ነቢያትን እጠላለሁ፤ ይህን ሕልም እየተናገሩ ሐሰት በተሞላ ትምክሕታቸው ሕዝቤን ከእውነተኛ መንገድ ያወጣሉ፤ እኔ አላክኋቸውም፤ ወይም ሂዱልኝ አላልኳቸውም፤ ለሕዝቡም የሚሰጡት ጥቅም የለም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እኔም ይህንኑ ለሐናንያ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ አንተን እኮ እግዚአብሔር አላከህም፤ ይህንንም ሁሉ ሕዝብ ሐሰት በሆነ ነገር እንዲተማመን አድርገሃል።
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”
‘ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! እኛም በሰላም እንኖራለን!’ በምትሉት ከንቱ ቃላችሁ አትታመኑ።
ስለዚህ እርሻቸውን ሁሉ ለሌሎች ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ ሚስቶቻቸውንም ሌሎች ወንዶች እንዲቀሙአቸው አደርጋለሁ፤ ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው በማታለል ጥቅምን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤