ኤርምያስ 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፦ ‘በመሠዊያችሁ ላይ የምታቀርቡትን የሚቃጠለውንም ሆነ ሌላውን መሥዋዕታችሁን ሰብስባችሁ ሥጋውን ለራሳችሁ ብሉት።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን በሌሎች መሥዋዕታችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሌላ መሥዋዕቶቻችሁ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፥ ሥጋውንም ብሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከቍርባናችሁ ጋር የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፤ ሥጋውንም ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሌላ መሥዋዕታችሁ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፥ ሥጋውንም ብሉ። |
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑ በጎቻችሁን አላቀረባችሁልኝም፤ በመሥዋዕታችሁም አላከበራችሁኝም፤ እኔም መባ እንድታቀርቡልኝ በመጠየቅ ሸክም አልሆንኩባችሁም፤ ‘ዕጣን አቅርቡልኝም’ ብዬ አላሰለቸኋችሁም።።
እየጾሙ ቢጸልዩ እንኳ አላዳምጣቸውም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የእህል ቊርባን ቢያቀርቡልኝ እንኳ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”
ከሳባ የሚያመጡልኝ ዕጣን፥ ከሩቅ አገሮች የሚያመጡልኝ ቅመማቅመም ሁሉ ለእኔ ምን ይረባኛል? መባቸውን አልቀበለውም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘኝም።
“እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?
እነርሱ ለእኔ ምርጥ መሥዋዕት ቢያቀርቡ፥ የመሥዋዕቱንም ሥጋ ቢበሉ እኔ እግዚአብሔር አልቀበላቸውም። አሁን በደላቸውን አስቤ በኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን፥ ማለትም ሥጋውንና ደሙን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የሌሎች መሥዋዕቶችህ ደም ከአምላክህ ከእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን ልትበላ ትችላለህ።