ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።
ኤርምያስ 6:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይህ ሕዝብ ተሰናክሎ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ አባቶችና ልጆች፥ ጓደኛሞችና ጐረቤቶች በአንድነት ይሞታሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክልን አስቀምጣለሁ፤ አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድነት ይደናቀፉበታል፤ ጎረቤቶችና ባልንጀሮችም ይጠፋሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፥ ከዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ፤ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፥ ጎረቤትና ባልንጀራውም ይጠፋሉ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳድራለሁ፤ አባቶችና ልጆችም በአንድነት ይታመማሉ፤ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ፥ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፥ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ። |
ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።
ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
አምላክ ሆይ! አሁን ግን ልጆቻቸው በራብ እንዲያልቁ፥ እነርሱም በጦርነት እንዲወድቁ አድርግ፤ ሴቶቻቸው ያለ ባልና ያለ ልጅ ይቅሩ፤ ወንዶቻቸው በበሽታ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ይደምሰሱ።
አምላክ ሆይ! እነርሱ እኔን ለመግደል የሸረቡትን ሤራ ታውቀዋለህ፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ይቅር አትበል፤ ኃጢአታቸውም እንዲሰረይላቸው አታድርግ፤ በፊትህ እንዲሸነፉና በብርቱ ቊጣህ እንዲወድቁ አድርግ።”
አንተና መኳንንትህ ከወረርሽኝ፥ ከጦርነትና ከራብ የሚተርፉትንም ሕዝብ በሙሉ በንጉሥ ናቡከደነፆርና ሊገድሉህ በሚፈልጉህ ጠላቶችህ እንድትማረኩ አደርጋለሁ፤ እርሱም ምሕረት ወይም ርኅራኄ በማሳየት አንድ ሰው እንኳ አይተውልህም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
ሕዝቤ ሆይ! ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ስታደርጉ ጥቂት ኀፍረት ተሰምቶአችሁ ነበርን? ኀፍረት ሊሰማችሁ ቀርቶ ዐይናችሁ እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እናንተም ትወድቃላችሁ፤ እኔ በምቀጣችሁ ጊዜ ፍጻሜአችሁ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
“በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ክፉ ሥራ መሥራት ቢጀምርና እኔም በችግር ላይ እንዲወድቅ ባደርገው፥ አንተ ካላስጠነቀቅኸው በቀር በኃጢአቱ ይሞታል፤ ከዚያ በፊት የፈጸመው መልካም ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ስለ እርሱ ሞት አንተን በኀላፊነት እጠይቅሃለሁ።
በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።
ማንም ሳያሳድዳቸው ከጠላት እንደሚሸሹ ሆነው አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ተሰነካክለው ይወድቃሉ፤ ማንኛውንም ጠላት ተቋቊማችሁ ለመዋጋት አትችሉም።
ይህም፦ “እነሆ፥ ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ ይህም ድንጋይ ሰዎችን በማሰናከል የሚጥል አለት ነው፤ በእርሱ የሚያምን ግን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።