ኤርምያስ 52:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በመምጣት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል አስከበባት፤ ሠራዊቱም በከተማይቱም ዙሪያ ሰፈረ፤ በቅጥሩም ዙሪያ ዐፈር ቈለለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ከተማዪቱንም ከበቧት፤ በዙሪያውም የዐፈር ድልድል ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት በዙሪያዋም ለመክበብያ የሚሆን ምሽግ ሠሩባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት በዙሪያዋም ዕርድ አደረገ። |
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከነሠራዊቱ ከተማይቱን ለመውጋት በመክበብ ላይ ይገኛል፤ ስለዚህ ምናልባት በረድኤት ከእኛ ጋር ሆኖ ድንቅ ሥራውን በመግለጥ ናቡከደነፆርን እንዲመለስ ያደርግልን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠይቅልን።”
“እነሆ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ለመያዝ ዐፈር ቈልለው ዙሪያዋን በመክበብ ላይ ናቸው፤ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር ከተማይቱ በእነርሱ እጅ እንድትወድቅ ያደርጓታል፤ እነሆ አንተ የተናገርከው ሁሉ መድረሱን ታያለህ፤
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በግዛቱ ሥር ባሉት መንግሥታትና ሕዝቦች ጭምር እየተረዳ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ላይ የጦርነት አደጋ በሚጥልበት ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ አደረገ።
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ከበው ሳለ ወታደሮቹ በሌሊት አምልጠው ነበር፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ በሚወስደው መንገድ በኩል በማለፍ ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው በቅጽር በር ወጥተው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፤
እነሆ ቀኝ እጁ ‘ኢየሩሳሌም!’ የሚል ጽሑፍ ያለበትን ፍላጻ አንሥቶ ይይዛል፤ እርሱም ሄዶ ምሽግ ማፍረሻዎችን እንዲያዘጋጅ፥ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ድንፋታ እንዲያሰማ፥ ምሽግ ማፍረሻዎችን ወደ ቅጽር በሮቹ እንዲያስጠጋ፥ ዐፈር ቈልሎ እንዲደለድልና የከበባ ምሽግ እንዲሠራ ይነግረዋል።
ጥፋት! ጥፋት! አዎ በእርግጥ ከተማይቱ እንድትጠፋ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን ከተማይቱን እንዲቀጣ የመረጥኩት እስከሚመጣ ድረስ ይህ አይሆንም፤ በዚያን ጊዜ ለእርሱ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።
በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል።
በተሰደድን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ ዐሥረኛው ወር በገባ በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም አምልጦ የመጣ አንድ ሰው ከተማይቱ በጠላት እጅ መውደቋን ነገረኝ።
በተሰደድን በሃያ አምስተኛው ዓመት፥ ኢየሩሳሌምም በጠላት እጅ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፥ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ እርሱም ብድግ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደኝ፤
ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማፍረሳችሁ እናንተን ለመቅጣት ጦርነት አመጣባችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ብትሰበሰቡም ሊፈወስ የማይችል በሽታ በመካከላችሁ እልካለሁ፤ ለጠላቶቻችሁም እጃችሁን ለመስጠት ትገደዳላችሁ።
“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”