ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ።
ኤርምያስ 51:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማሕሴያ የልጅ ልጅ የሆነው የኔሪያ ልጅ ሠራያ የንጉሥ ሴዴቅያስ የቅርብ አገልጋይ ነበር፤ ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ሠራያ ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን ወረደ፤ እኔም ኤርምያስ በዚያን ጊዜ መመሪያዎችን ሰጠሁት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ የንጉሡ የግቢ አስከልካይ የነበረው የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ ከንጉሡ ጋራ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የሰጠው መልእክት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የሻለቃ መጋቢ ባሻ አዛዥ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ዘንድ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ለማሴው ልጅ ለኔርዩ ልጅ ለሠራያ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የቤት አዛዥ ነበረ። |
ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ።
በዚሁ ዘመን፥ ማለትም ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር የገባዖን ሰው የሆነው የዐዙር ልጅ ሐናንያ በቤተ መቅደስ ተናገረኝ፤ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦
የማሕሴያ የልጅ ልጅ ለሆነው ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እነዚያን ግልባጮች የሰጠሁት በሐናምኤል፥ የሽያጩን ውል በፈረሙት ምስክሮችና በአደባባዩ ተቀምጠው በነበሩት ሰዎች ፊት ነው፤
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አንድ ዓመት ነበር፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ የእናቱም ስም ሐሙጣል ይባል ነበር፤ እርስዋም የሊብናው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።