ኤርምያስ 51:59 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)59 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ዘንድ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ለማሴው ልጅ ለኔርዩ ልጅ ለሠራያ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም59 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ የንጉሡ የግቢ አስከልካይ የነበረው የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ ከንጉሡ ጋራ ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የሰጠው መልእክት ይህ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)59 የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የሻለቃ መጋቢ ባሻ አዛዥ ነበረ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም59 የማሕሴያ የልጅ ልጅ የሆነው የኔሪያ ልጅ ሠራያ የንጉሥ ሴዴቅያስ የቅርብ አገልጋይ ነበር፤ ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ሠራያ ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን ወረደ፤ እኔም ኤርምያስ በዚያን ጊዜ መመሪያዎችን ሰጠሁት፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)59 የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የቤት አዛዥ ነበረ። Ver Capítulo |