ኤርምያስ 51:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባቢሎንን ማንም የማይኖርባት ምድረ በዳ እንድትሆን ለማድረግ እግዚአብሔር ያቀደውን የሚፈጽምበት ጊዜ ከመሆኑ የተነሣ፥ ምድር በመናወጥ ትንቀጠቀጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በዚያ መኖር እስከማይችል ድረስ፣ የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደው ስለሚጸና፣ ምድር ትናወጣለች፤ በሥቃይም ትወራጫለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ የጌታ አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች ተወራጨችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር ዐሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች፤ ታመመችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናውጣለች ታመመችም። |
ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
አሁን እንግዲህ እግዚአብሔር በባቢሎናውያን ላይ የመከረውን ምክርና በከለዳውያን ምድር ላይ ያቀደውን ዕቅድ ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች ተጐትተው ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸው አስደንጋጭ ይሆናል።
ለማእዘን ወይም ለመሠረት የሚያገለግል ድንጋይ አይገኝብሽም፥ አንቺ ለዘለዓለሙ ምድረ በዳ ትሆኚአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ፤ መድቡ፤ ወደ ሜዶን ነገሥታት፥ ወደ መሪዎቻቸውና ጦር አዛዦቻቸው እንዲሁም እነርሱ በሚቈጣጠሩአቸው አገሮች ወደሚኖሩ ሠራዊት ሁሉ መልእክት ላኩ።
ያቺ አገር የፍርስራሽ ክምርና የቀበሮዎች መፈንጫ ትሆናለች፤ ለማየትም የምታሰቅቅ ትሆናለች፤ ማንም አይኖርባትም፤ የሚያያትም ሁሉ ይሳለቅባታል።
ጠላቶቻችን እስከ ዳን ከተማ ደርሰዋል፤ ፈረሶቻቸው ሲያንኮራፉ ድምፃቸው ይሰማል፤ ሰንጋ ፈረሶቻቸውም ሲያሽካኩ ምድር ትናወጣለች፤ ጠላቶቻችን የመጡት ምንም ሳያስቀሩ ሕዝባችንንና ከተሞቻችንን እንዲሁም በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው።”
ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!