ኤርምያስ 50:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጎች የአውሬ ሰለባ እንደሚሆኑ እነርሱንም ያገኛቸው ሁሉ አደጋ ጣለባቸው፤ ጠላቶቻቸውም ‘እኛ እኮ ምንም አልበደልንም፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእነርሱ ላይ የደረሰባቸው የቀድሞ አባቶቻቸው ተስፋ አድርገውበት በኖሩት አምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት ነው፤ እነርሱም እንደ አባቶቻቸው ለእርሱ ታማኞች ሆነው መኖር ይገባቸው ነበርና ነው።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤ ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤ እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣ እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያገኙአቸው ሁሉ አጠፉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በጌታ ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በጌታ ላይ እነርሱ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም፥ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፤ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠሩ እኛ አናሳርፋቸውም አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም አሉ። |
እኔ በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እነርሱንም እንደ ርኩስ ቈጥሬ፥ ለአንቺ አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን ርኅራኄ አላደረግሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ሰዎች ላይ የጭቈና ቀንበር አበዛሽባቸው።
እርሱ ከምሥራቅ ሶርያውያንን፥ ከምዕራብ ፍልስጥኤማውያንን ልኮ እስራኤልን እንዲወሩ አደረገ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ቊጣው አልበረደም፤ ስለዚህ እጁ እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተቃጣ ነው።
ቊጣህን አንተን በማያውቁና ስምህን በማይጠሩ ሕዝቦች ላይ አፍስሰው፤ እነርሱ ሕዝብህን ፈጅተዋል፤ ሁላችንንም ፈጽመው በመደምሰስ፥ አገራችንን አውድመዋል።
የእስራኤል ተስፋ አንተ ብቻ ነህ፤ ከመቅሠፍት የምታድነንም አንተ ነህ፤ ታዲያ በምድራችን እንደ እንግዳ፥ ለአንድ ቀን እንደሚያድር መንገደኛስ የሆንከው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።
እስራኤል ሆይ! አንቺ እንደ መከር መጀመሪያ ፍሬ ለእኔ የተለየሽ ነበርሽ፤ ለእኔም የተቀደስሽ ርስት ሆነሽ ነበር፤ ስለዚህም አንቺን መጒዳት በሚፈልጉት ሁሉ ላይ መከራና መቅሠፍት አመጣሁባቸው።’ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን ወደ አገራቸው በመለስኩ ጊዜ በይሁዳና በከተሞቹ እንደገና ‘አንቺ የእውነት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ተራራ እግዚአብሔር ይባርክሽ’ ይላሉ።
በዚያን ጊዜ የዳዊት ዘር ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ጻድቅ ንጉሥ እመርጣለሁ፤ ያም ንጉሥ በአገሪቱ ላይ ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል፤ ትክክለኛ ፍርድም ይሰጣል።
ሰብላችሁንና ምግባችሁን ሁሉ ጠራርገው ይበሉታል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ሁሉ ይገድላሉ፤ የበጎችና የከብት መንጋችሁን ሁሉ ያርዳሉ፤ የወይን ተክሎቻችሁንና የበለስ ዛፎቻችሁን ሁሉ ያጠፋሉ፤ ሠራዊታቸውም የምትተማመኑባቸውን የተመሸጉ ከተሞቻችሁን ሁሉ ያወድማሉ።
“እናንተ ቀስተኞች ባቢሎንን ለመውጋት ዙሪያዋን ክበቡ፤ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ስለ ሠራች ፍላጾቻችሁንም ሁሉ በባቢሎን ላይ ወርውሩ፤ ለፍላጾቻችሁ አትሳሱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል ሕዝብ አንበሳ እያባረረ እንደሚበትናቸው በጎች ሆነዋል፤ በመጀመሪያ አውሬ ያደነውን ሁሉ ቦጫጭቆ እንደሚበላ የአሦር ንጉሥ እነርሱን ፈጃቸው፤ ከዚያም በኋላ አንበሳ አጥንትን እንደሚቈረጣጥም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አደቀቃቸው።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቊነዋል፤ ማርከው የወሰዱአቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤ ሊለቁአቸውም አልፈለጉም።
እነርሱ ባድማ የተደረጉ ስለ ሆነ በእኛ ቊጥጥር ሥር እንዲሆኑ ተሰጥተውናል’ ብላችሁ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የተናገራችሁትን የንቀት ንግግር እኔ እግዚአብሔር የሰማሁ መሆኔን ወደፊት ታውቃላችሁ።
ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል።
ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።
የገዙአቸው ሰዎች በጎቹን በማረዳቸው አይቀጡበትም፤ የሸጡአቸውም ሰዎች ‘እግዚአብሔር ይመስገን በልጽገናል’ ይላሉ፤ እረኞቻቸው እንኳ ለእነርሱ አይራሩላቸውም።”