ኤርምያስ 50:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣ በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ! ለዝርፊያም ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ ሰይፍም በመዝገብዋ ላይ አለ ለብዝበዛም ይሆናል። |
የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤
በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ።
ከየአቅጣጫው ዝመቱባት፤ እህልዋ የተከማቸበትን ጐተራ ሁሉ ክፈቱ፤ ምርኮውንም እንደ እህል ምርት ቈልሉት፤ ምንም ነገር ሳትተዉ አገሪቱን አጥፉ!
የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።
“ያም ጦርነት ከኢትዮጵያ፥ ከሊብያ፥ ከልድያ፥ ከሊቢያ፥ ከዐረብ አገር፥ በቃል ኪዳን የእኔ ወገኖች ከሆኑት ሕዝብ መካከል እንኳ ተቀጥረው የመጡትን ሁሉ የሚፈጅ ይሆናል።”
እኔ ከማቀርብላቸው ማእድ የፈረሶችንም ሆነ የፈረሰኞችን፥ የወታደሮችንም ሆነ የሌሎችን ጦረኞች ሥጋ እስከሚጠግቡ ይመገባሉ፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤