Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 46:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርሱ በመላው ዓለም የሚካሄደውን ጦርነት ሁሉ ያቆማል፤ ቀስትንና ጦርን ይሰብራል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የጌታን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 46:9
13 Referencias Cruzadas  

እርሱ በብዙ መንግሥታት መካከል በመፍረድ አለመግባባትን ያስወግዳል፤ ስለዚህም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያም በኋላ የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀደም ብዬ ግን ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።


በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።


የኀያላን ቀስቶች ተሰበሩ፤ ደካሞች ግን ብርታትን አግኝተው ጠነከሩ፤


ኢያሱም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። ይኸውም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ቈረጠ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።


ከዚያም በኋላ እርሱን መትቼ ቀስቱን ከግራ እጁ፥ ፍላጻውንም ከቀኝ እጁ አስጥለዋለሁ።


እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።


እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ኑ እዩ፤ እርሱ ለሰው ልጆች ድንቅ ሥራ ሠርቶአል።


አዎ! የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በሀገሪቱ በሞላ ቊርጥ ውሳኔ የሰጠበትን የጥፋት ፍርድ ያመጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios