ኤርምያስ 48:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠፍ እንድትሆን በሞአብ አገር ላይ ጨው ነስንሱባት፤ ከተሞችዋም ሰው የማይኖርባቸው ባድማ ይሆናሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርራ እንድታመልጥ፣ ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤ ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣ ባድማ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ሰው የማይኖርባቸው ባድማ ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በርራ እንድትወጣ ለሞአብ ክንፍ ስጡአት፤ ከተሞችዋም ባድማ ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸውም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርራ እንድትወጣ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት፥ ከተሞችዋም ባድማና ወና ይሆናሉ። |
የአርኖንን ወንዝ የሚሻገሩ የሞአብ ሴቶች ከጎጆዎቻቸው ተበታትነው ክንፎቻቸውን እያራገቡ ወዲያና ወዲህ እንደሚንከራተቱ የወፍ መንጋዎች ናቸው።
እነሆ በአሁኑ ጊዜ ምድራችሁ ፍርስራሽ ሆናለች፤ የሚኖርባትም የለም፤ ምድሪቱ አጸያፊ ሆናለች፤ ሕዝብም ሁሉ እንደ ተረገመች ይቈጥሩአታል፤ እግዚአብሔር የዐመፅና የክፋት ሥራችሁን ሁሉ አይታገሥም።
እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”
ሴቲቱ በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ የታላቅ ንስር ክንፎች የሚመስሉ ሁለት ክንፎች ተሰጡአት፤ እዚያም ከእባቡ ፊት ርቃ ሦስት ዓመት ተኩል በእንክብካቤ ተይዛ ትጠበቅ ነበር።