ኤርምያስ 48:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብን እንደማይፈለግ ዕቃ ስለ ሰበርኳት በቤት ሰገነቶች ላይና በሕዝብ አደባባዮች ሁሉ ከለቅሶ በቀር ሌላ የሚሰማ ነገር የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፣ በሕዝብም አደባባዮች፣ ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤ እንደማይፈለግ እንስራ፣ ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብን ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ሰብሬዋለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞአብንም ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞአብ ሰገነት ሁሉ ላይ፥ በአደባባዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብን እንደማይወደድ ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
የሠራዊት አምላክ እንድነግራቸው ያዘዘኝም ቃል ይህ ነው፥ “ይህ የተሰበረ የሸክላ ገንቦ ተመልሶ ሊጠገን እንደማይችል፥ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ በዚሁ ዐይነት እሰባብራለሁ፤ ሰዎች ሙታናቸውን የሚቀብሩበት ሌላ ስፍራ ስለማይገኝ በቶፌት ይቀብሩአቸዋል።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”
“እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ።