ዮርዳኖስንም ተሻግረው በጋድ ውስጥ በሚገኘው ሸለቆ መካከል ባለችው በዓሮዔር ከተማ በስተ ደቡብ ሰፈሩ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን አምርተው ወደ ያዕዜር ደረሱ፤
ኤርምያስ 48:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓሮዔር የምትኖሩ ሁሉ፥ በመንገድ ዳር ቆማችሁ ተጠባበቁ፤ የሚሸሹትን ወንዶችና የሚያመልጡትን ሴቶች ሁሉ በመጠየቅ፥ የሆነውን ነገር ሁሉ ዕወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል?፥ ብለሽ ጠይቂ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፥ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፥ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂ። |
ዮርዳኖስንም ተሻግረው በጋድ ውስጥ በሚገኘው ሸለቆ መካከል ባለችው በዓሮዔር ከተማ በስተ ደቡብ ሰፈሩ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን አምርተው ወደ ያዕዜር ደረሱ፤
ከዩኤል ጐሣ የሼማዕ የልጅ ልጅ የዓዛዝ ልጅ የሆነው ቤላዕ ናቸው፤ ይህም ጐሣ ይኖር የነበረው በዓሮዔርና ከዚያም በስተሰሜን እስከ ነቦና እስከ ባዓልመዖን ባለው ግዛት ነበር፤
በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤
ስለዚህ ሦስት መቶ ዓመት ሙሉ እስራኤል ሐሴቦንና መንደሮችዋን ዓሮዔርንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም በአርኖን ወንዝ ዳርቻ ያሉትን ከተሞች በሙሉ ወርሰው ኖረዋል፤ ታዲያ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ስለምን መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር?
ሰውየውም ቀርቦ “እኔ ከጦርነቱ አምልጬ መጣሁ፤ ዛሬም እዚህ የደረስኩት በብርቱ ሩጫ ነው” አለ። ዔሊም “ልጄ ሆይ! ታዲያ እንዴት ሆነ?” አለው።