ኤርምያስ 44:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌምን በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር እንደቀጣሁ፥ በግብጽ የሚኖሩትንም እቀጣለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሩሳሌምን እንደ ቀጣሁ፣ በግብጽ የሚኖሩትን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እቀጣለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሩሳሌምን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንደ ቀጣሁ፥ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን እቀጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሩሳሌምንም በመዐት እንደ ጐበኘሁ፥ እንዲሁ በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እጐበኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሩሳሌምንም እንደ ቀጣሁ፥ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ። |
በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት ወይም በራብ፥ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ አሁን ከተማይቱን ከበው ወዳሉት ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይሞትም፤ ሌላው ቢቀር ሕይወቱን ያተርፋል፤
በስደት እንዲበታተኑ ባደረግሁባቸው በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ የተጠሉ፥ የተሰደቡ፥ የመነጋገሪያ ርእስ የሆኑ፥ መሳለቂያና የተወገዙ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።
እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚለውን ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በዚያ ለመኖር ብትወስኑ፥
ወደ ግብጽ ሄደው ለመኖር የወሰኑ ሁሉ፥ በጦርነት ወይም በራብ ወይም በወረርሽኝ ያልቃሉ፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ አይተርፍም፤ በእነርሱ ላይ ላመጣው ካቀድኩት መቅሠፍትም የሚያመልጥ አይኖርም።’
“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ እንሄዳለን ብላችሁ ብትወስኑ ከዚህ በፊት በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የወረደው ቊጣዬና መዓቴ በእናንተም ላይ ይወርዳል፤ ለሕዝብ ሁሉ አስፈሪ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፤ የሚያዩአችሁም ሕዝብ ሁሉ መዘባበቻ ያደርጓችኋል፤ ስማችሁም ለመሳለቂያ ይሆናል፤ ይህችንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩአትም።’ ”
ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን ድል ይነሣል፤ በበሽታ እንዲሞቱ የተወሰነባቸው በበሽታ ይሞታሉ፤ ተማርከው እንዲወሰዱ የተወሰኑ ይማረካሉ፤ በጦርነት እንዲሞቱ የተወሰኑ በጦርነት ይገደላሉ።
እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።