ይኸውም ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ኤርምያስ 38:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም እንዲህ አልኩት፦ “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ይወሰዳሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ ተይዘህ እስረኛ ትሆናለህ፤ ከእነርሱ እጅ ከቶ አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ተቃጥላ ትወድማለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ተወስደው ለባቢሎናውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ራስህ በባቢሎን ንጉሥ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፥ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፥ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች። |
ይኸውም ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ይህች ከተማ እንድትጠፋ ወስኛለሁ፤ ፈጽሞም ምሕረት አላደርግላትም፤ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
አንተም ማምለጥ አትችልም፤ ትማረካለህ፤ ለእርሱም ተላልፈህ ትሰጣለህ፤ እርሱን በቀጥታ ፊት ለፊት ታየዋለህ፤ እርሱም ያነጋግርሃል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤
ነገር ግን የባቢሎን ሠራዊት ከኋላቸው ተከትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ደረሱበትና ሴዴቅያስን ማረኩት፤ ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር በሐማት ግዛት ሪብላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ውስጥ ነበር፤ ንጉሥ ናቡከደነፆርም እዚያው በሴዴቅያስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈበት።
ከዚያም በኋላ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የቀሩትንም ሕዝብ በምጽጳ አሰረ፤ እነዚህም ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ ጦር አዛዥ ናቡዛርዳን በገዳልያ ሥር እንዲጠበቁ ዐደራ የተሰጡ ነበሩ፤ እስማኤል ግን እነዚህን ሁሉ ማርኮ ወደ ዐሞን ግዛት አቅጣጫ ተሻገረ።
“አንድ ነቢይ ተጠይቆ ሐሰተኛ መልስ ለመስጠት ቢነሣሣ እኔ እግዚአብሔር ያን እንዲያደርግ እተወዋለሁ። ይህንንም ካደረገ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አጠፋዋለሁ።
ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ዐምፆ ፈረሶችንና ታላቅ ሠራዊት እንዲያመጡለት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ታዲያ ይህ ዕቅዱ ይሳካለታልን? በዚህስ ሊያመልጥ ይችላልን? ውሉን የሚያፈርስ ከሆነ ከቅጣት ከቶ ያመልጣልን?
ይህም ራእይ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ይመስል ነበር፤ በኬባር ወንዝ አጠገብ ካየሁትም ራእይ ጋር ይመሳሰላል፤ በዚያን ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ።