“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።
ኤርምያስ 29:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በእነርሱ ላይ ጦርነትን፥ ራብንና ቸነፈርን ላመጣባቸው ነው፤ ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበሉት እንደማይቻል የበለስ ዛፍ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በርግጥ እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍን፣ ራብንና መቅሠፍትን እሰድድባቸዋለሁ፤ ከመበላሸቱ የተነሣም ሊበላ እንደማይቻል እንደ መጥፎ የበለስ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም በመካከላቸው እልክባቸዋለሁ፥ ከክፋቱም የተነሣ ሊበላ እንደማይችል እንደ ተበላሸ በለስ አደርጋቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይፍንና ራብን፥ ቸነፈርንም እሰድድባቸዋለሁ፤ ከመጐምዘዙም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍንና ራብን ቸነፈርንም እሰድድባቸዋለሁ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ። |
“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።
በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር አባርራቸዋለሁ፤ የዓለም ሕዝብ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስለሚያዩት ነገር ይደነግጣሉ፤ እንዲበተኑ በማደርግበት ስፍራ ሁሉ በእነርሱ ላይ የማደርሰውን ነገር የሚያዩ ሕዝቦች ሁሉ በመደንገጥ ይሸበራሉ። ሕዝብም ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ያደርጋቸዋል።
“እነሆ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ለመያዝ ዐፈር ቈልለው ዙሪያዋን በመክበብ ላይ ናቸው፤ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር ከተማይቱ በእነርሱ እጅ እንድትወድቅ ያደርጓታል፤ እነሆ አንተ የተናገርከው ሁሉ መድረሱን ታያለህ፤
ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን ድል ይነሣል፤ በበሽታ እንዲሞቱ የተወሰነባቸው በበሽታ ይሞታሉ፤ ተማርከው እንዲወሰዱ የተወሰኑ ይማረካሉ፤ በጦርነት እንዲሞቱ የተወሰኑ በጦርነት ይገደላሉ።
በዚያን ጊዜ ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ እመጫቶች ወዮላቸው! በምድር ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣል።
እነሆ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ይባል ነበር፤ ሲኦልም ይከተለው ነበር፤ ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ እጅ በጦርነት፥ በራብ፥ በቸነፈርና በምድር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።