የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።
ኤርምያስ 28:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ስለ ሰላም የተናገረ ነቢይ ቢኖር ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ መሆኑ የሚታወቀው ያ የተናገረው ትንቢት እውነት ሆኖ ሲገኝ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይ እግዚአብሔር በእውነት እንደ ላከው የሚታወቀው የተናገረው ትንቢት ሲፈጸም ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ሰላም የተናገረ ነቢይ፥ የነቢዩ ቃል በሆነ ጊዜ፥ ጌታ በእውነት የላከው ነቢይ እንደሆነ ይታወቃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ሰላም ትንቢት የተናገረ ነቢይ ትንቢቱ በደረሰ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእውነት የላከው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሰላም የተናገረ ነቢይ፥ የነቢዩ ቃል በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእውነት የሰደደው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል። |
የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ነቢያቱ ‘ጦርነት ሆነ ራብ አይኖርም’ እያሉ ለሕዝቡ ይናገራሉ፤ ‘በምድራችን ዘላቂ ሰላም ብቻ እንደሚሰፍን እግዚአብሔር ተናግሮአል’ ይላሉ።”
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ቃሉ ሳይፈጸም ቢቀር ያ ትንቢት ነቢዩ በግምት የተናገረው ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት የተናገረው ቃል ስላልሆነ ልትፈራው አይገባም።