ኤርምያስ 13:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን እግዚአብሔር የበረሓ ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ይበታትናችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የበረሓ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ፣ እንዲሁ እበታትናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፋስ በምድረ በዳ እንደሚበትነው እብቅ እበትናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ። |
ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።
ወደ ሰማይ ትበትናቸዋለህ፤ ነፋስም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእኔ በእስራኤል ቅዱስም ትመካለህ።
ትቢያ በምሥራቅ ነፋስ እንደሚበተን፥ ሕዝቤን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። ፊቴን ከእነርሱ መልሼ ጀርባዬን እሰጣቸዋለሁ። ጥፋት በሚመጣባቸውም ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።”
“እግዚአብሔር ወታደሮቻችንን ከእኛ አስወገደ፤ የጐልማሶቻችንን ኀይል ለማድቀቅ የጦር ሠራዊት ላከብን፤ እግዚአብሔር ባልተደፈረችው ከተማ የሚኖረውን ሕዝባችንን በወይን መጭመቂያ እንደሚረገጥ የወይን ዘለላ ረገጣቸው።
ምርጥ የሆኑ ወታደሮቹ በጦር ሜዳ ይገደላሉ፤ ከሞት የሚያመልጡትም በየአቅጣጫው ይበተናሉ፤ በዚያን ጊዜ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
ከበባው ከተፈጸመ በኋላ ከሦስቱ አንዱን እጅ የከተማውን ንድፍ በሠራህበት ጡብ መካከል አቃጥለው፤ ሁለተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ቈራርጠህ የከተማው ንድፍ በተሠራበት ጡብ ዙሪያ አኑረው። ሦስተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
“ነገር ግን ጥቂቶቻችሁ እንድትተርፉ አደርጋለሁ፤ ጥቃቶቻችሁ ወደ ሌሎች ሕዝቦች በመሄድ ከጦርነት አምልጣችሁ በተለያዩ አገሮች ትበተናላችሁ።
በዚህም ምክንያት እነርሱ እንደ ማለዳ ጉም ተነው ይጠፋሉ፤ እንደ ጠዋት ጤዛም ይረግፋሉ፤ ከአውድማ ላይ በዐውሎ ነፋስ እንደሚጠረግ እብቅ ወይም በጢስ መውጫ ወጥቶ እንደሚያልቅ ጢስ ይሆናሉ።
በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤
አለበለዚያ ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ትሆናላችሁ፤ እንደ እሳት የሚነደው የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣባችኋል፤ ኀይለኛው የእግዚአብሔር የቊጣ ቀን ይመጣባችኋል።
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።