ኢሳይያስ 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር ዕቅድንም አውጡ፤ ነገር ግን እናንተ እንዳሰባችሁት አይሳካላችሁም፤ የፈለጋችሁትን ያኽል ተናገሩ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምክራችሁ አይጸናም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመካከሩ፥ ምክራችሁ ይፈታል፥ ቃሉን ተናገሩ፥ ቃሉም አይጸናም፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። |
ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
አኪጦፌል የሰጠው ምክር ተቀባይነት እንዳላገኘ በተረዳ ጊዜ አህያውን ጭኖ ወደ መኖሪያ ከተማው ተመልሶ ሄደ፤ ሁሉን ነገር መልክ በማስያዝ ካስተካከለም በኋላ ተሰቅሎ ሞተ፤ በቤተሰቡም መቃብር ተቀበረ።
ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።
የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”
የሠራዊት አምላክ ይህን ሁሉ ለማድረግ ወስኖአል፤ ይህ እንዳይሆን የሚያደርግ ማነው? ለመቅጣትም ክንዱን ዘርግቶአል፤ ተከላክሎ ሊያቆመው የሚችልስ ማን ነው?
ከሞት ጋር የገባችሁት ስምምነት ይቀራል፤ ከሙታን ዓለም ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤ መቅሠፍት በድንገት በሚመጣበት ጊዜ መጨረሻችሁ ይሆናል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
በኀይል እየጐረፈም ወደ ይሁዳ ምድር ይገባል፤ ሁሉን ነገር አጥለቅልቆ ከመሸፈን አልፎ ሙላቱ እስከ አንገት ይደርሳል፤” ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ እርሱም ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሰውራ እንደምትጠብቅ ምድሪቱን ይጠብቃል።
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የእግዚአብሔር መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ለሕዝቡ “ ‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ይላል እግዚአብሔር” ሲል የእግዚአብሔርን መልእክት አስተላለፈ።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
“ጠላቶችህን ለመውጋት ስትዘምት፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ ከአንተ የሚበልጥም ሠራዊት ባየህ ጊዜ ከግብጽ ምድር ያወጣህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ አትፍራቸው፤
አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤
ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።