ኢሳይያስ 53:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው፥ ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚያዞርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፥ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። |
በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።
“በእውነት እርሱ ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር ተመትቶ እንደ ወደቀና እንደ ቈሰለ አድርገን ቈጠርነው።
“እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤
እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እርግጥ ነው፤ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያስተካክላል፤ ይሁን እንጂ፥ የሰው ልጅ ከባድ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚናቅ የተጻፈው እንዴት ነው?
ቀጥሎም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል ይገባዋል፤ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፥ በሕግ መምህራን ዘንድ ይናቃል፤ ይገደላልም፤ ይሁን እንጂ በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።”
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።