ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።
ኢሳይያስ 47:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እነርሱንም እንደ ርኩስ ቈጥሬ፥ ለአንቺ አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን ርኅራኄ አላደረግሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ሰዎች ላይ የጭቈና ቀንበር አበዛሽባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴን አርክሼው ነበር፤ አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣ እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር ርስቴንም አረከስሁ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፥ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል። |
ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።
አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ።’ ”
የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ፥ ዖዴድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በሰማርያ ከተማ ይኖር ነበር፤ የእስራኤል ሠራዊት አይሁድን እስረኞች አድርገው በመውሰድ ወደ ሰማርያ ከተማ በመግባት ላይ ሳሉ ወደ እነርሱ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ ስለ ተቈጣ እነርሱን ድል እንድታደርጉአቸው አደረገ፤ እናንተ ግን ወደ ሰማይ በደረሰ ቊጣ ፈጃችኋቸው፤
ስለዚህ የባቢሎን ንጉሥ በእነርሱ ላይ አደጋ እንዲጥል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ንጉሡም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን እንኳ ሳይቀር፥ በይሁዳ የሚገኙትን ወጣቶች ወንዶችን ሁሉ በሰይፍ ፈጀ፤ እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር አሳልፎ ስለ ሰጣቸውም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ማንንም ሳይለይ፥ ሁሉንም ያለ ምሕረት አጠፋቸው።
በሰይፍ ከመገደል የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እነርሱም የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እስከ ተነሣበት ጊዜ ድረስ፥ በዚያው በባቢሎን ባሪያዎች ሆነው፥ ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የእርሱን ዘሮች ያገለግሉ ነበር።
ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ።
ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”
ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን ይዘዋል፤ እነርሱ ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፥ ድምፃቸው እንደሚተም ባሕር ነው፤ ባቢሎን ሆይ! እነርሱ በአንቺ ላይ አደጋ ለመጣል ለዘመቻ ተዘጋጅተው እንደሚመጡ ሰዎች ወደ አንቺ እየመጡ ነው።
“ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ።
ጌታ የእስራኤልን መኖሪያ ሁሉ ያለ ምሕረት አጠፋ፤ በቊጣውም የይሁዳን ሕዝብ ምሽግ አፈረሰ፤ መንግሥትዋንና ባለ ሥልጣኖቿን ወደ ምድር ጥሎ አዋረደ።
እግዚአብሔር ራሱ የበተናቸው ስለ ሆነ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ እነርሱ አያስብም፤ ለካህናቱ ክብር አይሰጣቸውም፤ ሽማግሌዎችም ልዩ አስተያየት አይደረግላቸውም።
‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።
በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።
ሕዝቤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ የመከራ ጽዋ ጠጥተዋል፤ በዙሪያው ያሉት አሕዛብ ሁሉ ከዚህ የከፋ የመከራ ጽዋ ይጠጣሉ፤ የጠጡትም ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።”
መልአኩም “የሠራዊት አምላክ ሆይ! ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ከተቈጣህ እነሆ ሰባ ዓመቶች አለፉ፤ ምሕረት የማታደርግላቸው እስከ መቼ ነው?” ሲል ጠየቀ።
ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።