Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ‘እኔ ለዘለዓለም ንግሥት ሆኜ እኖራለሁ’ አልሽ፤ ስላደረግሽው ድርጊት ምንም አላሰብሽም፤ የተግባርሽም ውጤት ምን እንደሚሆን አላስተዋልሽም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አንቺም፣ ‘እስከ መጨረሻው፣ ለዘላለም ንግሥት እሆናለሁ!’ አልሽ፤ ሆኖም እነዚህን ነገሮች አላስተዋልሽም፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደሚሆንም አላሰብሽም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አንቺም፦ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላደረግሽም ፍጻሜውንም አላሰብሽም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አን​ቺም፥ “እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እመ​ቤት እሆ​ና​ለሁ” ብለ​ሻል፤ ይህ​ንም በል​ብሽ አላ​ሰ​ብ​ሽም፤ ፍጻ​ሜ​ው​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ስ​ሽም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አንቺም፦ እኔ ለዘላለም እመቤት እሆናለሁ ብለሻል፥ ይህንም በልብሽ አላደረግሽም ፍጻሜውንም አላሰብሽም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:7
18 Referencias Cruzadas  

ምነው ብልኆች ሆነው ይህን ባስተዋሉና፤ መጨረሻውንም በተገነዘቡ ነበር!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤


ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”


ከዐሥራ ሁለት ወራት በኋላ ንጉሡ በባቢሎን በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ይመላለስ ነበር፤


ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ በወንዝ ውስጥ የተጋደመ አስፈሪ የባሕር አውሬ የምትመስል አንተ! እነሆ፥ እኔ በቊጣ ተነሥቼብሃለሁ፤ ‘የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ትላለህ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።


እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።


ጻድቃን ሲሞቱ ማንም ትኲረት አይሰጠውም፤ ደጋግ ሰዎች በሞት ሲወሰዱ ከክፉ ነገር እንዲድኑ የተወሰዱ መሆናቸውን ማንም ሰው ሊያስተውለው አይችልም።


“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?


አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች።


“የሰው ልጅ ሆይ! እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ምድር የምለው ይህ ነው፤ በሁሉም አቅጣጫ የዚህች ምድር የመጨረሻ መጥፊያ ደርሶአል።


“እኔ ናቡከደነፆር በቤተ መንግሥቴ በብልጽግናና በምቾት እኖር ነበር።


የሆነውን ነገር ሁሉ ከቁም ነገር ሳይቈጥረው ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios