ኢሳይያስ 38:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ እኛ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አውታር ባለው የሙዚቃ መሣሪያ የምሥጋና መዝሙር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዘምራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያድነኛል፤ ስለዚህ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ያድነኛል፤ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዬ ሆይ አንተ መድኀኒቴ ነህ፤ ስለዚህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አውታር ባለው ዕቃ አንተን ማመስገንን አላቋርጥም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ያድነኛል፥ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን። |
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።