ኢሳይያስ 27:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፥ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም። |
የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል።
የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።
በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ወጣቶቻቸውን ይቀጣል፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶችና አሳዳጊ ለሌላቸው ለሙት ልጆቻቸው አይራራም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ከሐዲና ክፉ አድራጊ ሆኖአል፤ ከእያንዳንዱም ሰው አንደበት የሚነገረው ቃል ተንኰል የሞላበት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እነርሱን ለመቅጣት እጁ እንደ ተቃጣ ነው።
አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ።
ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”
“ለቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ስለ ማንም ሐዘንህን አትግለጥ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝቤን በሰላም አልባርክም፤ ዘላቂ ፍቅርና ምሕረትም አላሳያቸውም፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
ሽመላዎች እንኳ የሚመለሱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ዋኖሶች፥ ጨረባዎች፥ ዋርዳዎችም በኅብረት የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ እናንተ ሕዝቤ ግን እንድትተዳደሩበት የሰጠኋችሁን ሕግ አታውቁም።
ነገር ግን በቊጣ ከስሩ ተነቅሎ ወደ ምድር ተጣለ። ከበረሓ የሚነሣ የምሥራቅ ነፋስ አደረቀው፤ ፍሬዎቹም ረገፉ፤ ብርቱ የሆኑት ቅርንጫፎቹም ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።
ለደቡብም ጫካ እኔ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ የሚለውን ስማ ብለህ ንገረው፤ ‘ተመልከት! እነሆ እኔ በውስጥህ እሳትን በማቀጣጠል ላይ ነኝ፤ ይህም እሳት ለምለሙንም ሆነ ደረቁን ሳይመርጥ ዛፎችን ሁሉ ያቃጥላል፤ እሳቱንም ሊያጠፋው የሚችል አይኖርም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ይዛመታል፤ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል።
ይሁን እንጂ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያት ምራቶቻችሁም አመንዝሮች ስለ ሆኑ አልቀጣቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ ወንዶች ራሳችሁ በቤተ መቅደስ የሚሴስኑ ሴቶችን ተከትላችሁ ከእነርሱ ጋር ባዕድ አምልኮ ትፈጽማላችሁ፤ ስለዚህ ማስተዋል የጐደለው ሕዝብ ይጠፋል።
ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።
የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ቃል ሰምቶ የማያስተውለውን ሰው ነው፤ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልቡ የተዘራውን ቃል ይወስድበታል፤
እነርሱን በጥንቃቄ ጠብቁአቸው፤ ይህንንም ስታደርጉ በሌሎች ሕዝቦች ዘንድ ምን ያኽል ብልሆችና አስተዋዮች መሆናችሁን ታሳያላችሁ። እነዚህም ሌሎች ሰዎች ስለ ደንቦቹ ሲሰሙ ይህ ትልቅ ሕዝብ በእውነት ብልኅና አስተዋይ ነው ይላሉ።
አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።