አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።
ኢሳይያስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ ወደ ጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ። |
አይሁድ ለራሳቸው፥ ለዘሮቻቸው አይሁዳዊ መሆን ለሚፈልግ ሁሉ ቋሚ ደንብ አደረጉ፤ ይኸውም በየዓመቱ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ መርዶክዮስ በሰጠው መመሪያ መሠረት እነዚህ ሁለት ቀኖች ባለማቋረጥ ይከበራሉ።
በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ የእነዚህ ሁለት አገር ሕዝቦች አንዱ ወገን ወደ ሌላ ይተላለፋሉ፤ የሁለቱም ሕዝቦች አምልኮ አንድ ዐይነት ይሆናል።
“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”
ለእነርሱ በቤተ መቅደሴና በግቢዬ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የተሻለ መታሰቢያ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ የማይረሳ ዘላቂ መታወቂያም እሰጣቸዋለሁ።”
“እነርሱን ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አምጥቼ በጸሎት ቤቴም ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ፤ በመሠዊያዬም ላይ የሚያቀርቡትን የሚቃጠልና ሌሎችን መሥዋዕቶች ሁሉ እቀበላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ቤቴ የሕዝቦች ሁሉ ጸሎት ቤት ተብሎ ስለሚጠራ ነው።”
“እኔን እግዚአብሔርን ትታችሁ የተቀደሰ ተራራዬን በመርሳት ‘መልካም አጋጣሚ’ ለተባለ ጣዖትም ማእድ ታዘጋጃላችሁ፤ ‘ዕድል ፈንታ’ ለተባለ ጣዖትም ዋንጫችሁን በተደባለቀ የወይን ጠጅ ትሞላላችሁ።
ወንድሞቻችሁን ሁሉ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቅዱስ ተራራዬ በፈረሶች፥ በሠረገሎች፥ በጋሪዎች፥ በበቅሎዎችና በግመሎች አድርገው ከተለያዩ አገሮች ለእግዚአብሔር እንደ መባ ያመጡአቸዋል፤ እነርሱንም የሚያመጡአቸው እስራኤላውያን የእህል ቊርባንን በሥርዓት በነጻ ዕቃ ለእኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ አድርገው ነው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
“ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የሞሬሼቱ ነቢይ ሚክያስ የሠራዊት አምላክ የተናገረውን የትንቢት ቃል ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ዐውጆ ነበር፦ ‘ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ኰረብታ ዳዋ ይበቅልበታል።’
በእግዚአብሔርም ራእይ ወስዶ በእስራኤል ምድር በአንድ ከፍተኛ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ እዚያም አንድ ብዙ ቤቶች የተሠሩበትን ከተማ የሚመስል ከተራራው በስተደቡብ በኩል አየሁ።
ከዚህ ጊዜ በኋላ እስራኤላውያን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርና ወደ ንጉሣቸው ወደ ዳዊት ይመለሳሉ፥ በኋለኛው ዘመን በፍርሃት ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፤ በረከቱንም ይቀበላሉ።
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፥ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ፥ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ፥ በሰማርያ፥ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
ስለዚህ ወዲያውኑ መልእክተኞች ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል፤ እንግዲህ እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት እዚህ ተሰብስበናል።”
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።
“አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።