ኢሳይያስ 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ የይሁዳ ነገሥታት ሆነው በነገሡባቸው ዘመናት የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፣ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፤ በኢዮአታም፤ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፤ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ። |
ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የያቤሽ ልጅ ሻሉም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ አንድ ወር ብቻ ገዛ።
ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሼብናንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፤
ኢዮአታም ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይሩሻ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች።
አካዝ ዕድሜው ኻያ ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም ምሳሌነትን ባለመከተሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አላደረገም፤
አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤ ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን “ጫማህንና የማቅ ልብስህን አውልቀህ በባዶ እግርህ ሂድ” ብሎ አዘዘው። ኢሳይያስም ለቃሉ በመታዘዝ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ይመላለስ ነበር።
አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።
የቤተ መንግሥቱን አዛዥ ኤልያቄምን፥ የቤተ መንግሥቱን ዋና ጸሐፊ ሼብናንና ከካህናት መካከል ታዋቂዎች የሆኑትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ማቅ ለብሰው ነበር።
በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለመሞት ተቃርቦ ነበር፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጐበኘው ወደ እርሱ ሄዶ “እግዚአብሔር ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ቤትህን አዘጋጅ’ ብሎሃል” ሲል ነገረው።
ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።
ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን አየሁት፤ እርሱም ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
ከዖዝያን ልጅ ከኢዮአታም የተወለደው አካዝ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን፥ የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የረማልያ ልጅ ፋቁሔ ጦርነት ማስነሣት ፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ድል ሊያደርጉአት አልቻሉም።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ነቢያቱ የሚሉትን አትስሙ፤ እነርሱ በሐሰተኛ ተስፋ ይሞሉአችኋል፤ የሚነግሩአችሁም በሐሳባቸው ያለሙትን እንጂ እኔ የምነግራቸውን ቃል አይደለም፤
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው።
ዖዝያን በይሁዳ፥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓምም በእስራኤል ላይ በነገሡበት ዘመን፥ በተቆዓ ከሚገኙ እረኞች አንዱ የሆነው አሞጽ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው።
እናንተም ማድረግ የምትፈልጉት ይህንኑ ስለ ሆነ፥ የምስጋና ቊርባን የሆነውን የኅብስት መባችሁን አቅርቡ፤ በፈቃዳችሁም ስለምታቀርቡት መሥዋዕት ዐዋጅ ንገሩ።”
ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በይሁዳ በነገሡበት ዘመን እግዚአብሔር ለሞሬታዊው ለሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ በገለጠለት ጊዜ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤
የግዚአብሔርን ቃል የሚሰማው ሰው የትንቢት ቃል ወድቆ ሳለ ዐይኖቹ ተከፍተው ሁሉን የሚችል አምላክን ራእይ የሚያይ ሰው መልእክት ይህ ነው።
ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤