Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢዮአታም ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይሩሻ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ ኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ስትሆን፣ ኢየሩሳ ትባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ኢየሩሳ ትባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢዮ​አ​ታ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ትባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ኢየሩሳ ትባል ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 27:1
9 Referencias Cruzadas  

አሜስያስ፥ ዐዛርያስ፥ ኢዮአታም፥


ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የቆዳው በሽታ አለቀቀውም፤ ይህም በመሆኑ በተለየ ቤት ኖረ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት እንዲገለል ተደረገ፤ ልጁ ኢዮአታም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በመሆን የአገሪቱን ሕዝብ ያስተዳድር ነበር።


ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ።


ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤


ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ የይሁዳ ነገሥታት ሆነው በነገሡባቸው ዘመናት የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፦


ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው።


ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በተከታታይ በይሁዳ በነገሡበት ዘመን እግዚአብሔር ለሞሬታዊው ለሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ በገለጠለት ጊዜ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦


ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤ አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos