Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ። ሕዝቡም “ለምጽ አለበት” ብለው የነገሥታቱ በሆነው መቃብር አጠገብ ባለው ቦታ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በምትኩ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ እነርሱም፦ “ለምጻም ነው” ብለው ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዖዝ​ያ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ለም​ጻም ነው ብለ​ዋ​ልና የነ​ገ​ሥ​ታቱ መቃ​ብር ባል​ሆነ እርሻ ውስጥ ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ለምጻም ነው ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር እርሻ ውስጥ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:23
7 Referencias Cruzadas  

ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።


እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።”


ኢዮአታም ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይሩሻ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች።


ንጉሥ አካዝ ሞተ፤ በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ።


ምናሴ ሞተ፤ በቤተ መንግሥቱም አጠገብ በሚገኘው ስፍራ ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ።


ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን አየሁት፤ እርሱም ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos