ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ሆሴዕ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጦርነት እንዲወጡ በገባዖን የመለከት፥ በራማም የጥሩንባ ድምፅ አሰሙ! በቤትአዌን “የብንያም ነገድ ሆይ! ከአንተ ጋር ነን” እያላችሁ ጩኹ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በጊብዓ መለከትን፣ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤ ‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኮረብታ ላይ መለከትን ንፉ፤ በተራሮችም ላይ ጩኹ፤ ብንያም በተዋረደበት በቤትአዌን ዐዋጅ ንገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጊብዓ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉና፦ ብንያም ሆይ፥ ከአንተ በኋላ እያላችሁ በቤትአዌን ላይ እሪ በሉ። |
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት ንፉ! ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደተመሸጉ ከተሞች እንዲሸሹ ንገሩአቸው።
የብንያም ሕዝብ ሆይ! ሕይወታችሁን ለማትረፍ ሽሹ! ከኢየሩሳሌምም ውጡ! በተቆዓ የጥሩምባ ድምፅ አሰሙ፤ በቤትሀካሬም ለምልክት የሚሆን እሳት አንድዱ! መቅሠፍትና ጥፋት ከሰሜን በኩል ሊመጣ ነው።
በሰማርያ ከተማ የሚኖሩ ሕዝቦች በቤትአዌን ስላለው በጥጃ ምስል በተሠራ ጣዖት በታላቅ ፍርሀት ይርበደበዳሉ፤ ክብሩ ስለ ተገፈፈ ሕዝቡ ያለቅሳሉ፤ የጣዖቱ ካህናትም እሪ ብለው ይጮኻሉ።
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እናንተ ብታመነዝሩም እንኳ የይሁዳ ሕዝብ በደለኛ እንዲሆን አታድርጉ፤ ወደ ጌልጌላ ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለ ተላለፉ በቤቴ ላይ ጠላት እንደ ጆፌ አሞራ ያንዣበበ ስለ ሆነ የማስጠንቀቂያ መለከት ንፉ!”
ለጦርነት የሚያዘጋጅ መለከት በከተማ ውስጥ ሲነፋ በፍርሃት የማይንቀጠቀጥ ሕዝብ ይኖራልን? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይመጣልን?
ኢያሱ በኢያሪኮ ሳለ በቤትአዌን አጠገብ ከቤትኤል በስተምሥራቅ የምትገኘውን “ዐይ” ተብላ የምትጠራውን ከተማና የምድሪቱን አቀማመጥ አጥንተው ይመለሱ ዘንድ ጥቂት ሰዎችን ላከ። ይህንንም በትእዛዙ መሠረት ከፈጸሙ በኋላ፥
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።