ዕብራውያን 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የጥምቀትን፥ የእጅ መጫንን፥ ከሞት የመነሣትን፥ የዘለዓለም ፍርድን ትምህርት እንደገና አንመሥርት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ስለ ጥምቀቶች፣ እጆችን ስለ መጫን፣ ስለ ሙታን ትንሣኤና ስለ ዘላለም ፍርድ ትምህርት እንደ ገና አንመሥርት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥምቀትን፥ በአንብሮተ እድ መሾምን፥ የሙታንን ትንሣኤና የዘለዓለም ፍርድን ለመማር ነው። |
ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።
ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።
እንዲሁም ከገበያ ሲመለሱ ካልታጠቡ አይበሉም ነበር፤ ዋንጫን፥ ማሰሮን፥ የናስ ዕቃዎችንና አልጋን፥ እንደማጠብ ያለ፥ ሌላም ብዙ ወግ ይጠብቁ ነበር።
ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
እኔ ራሴ አላውቀውም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ፥ ‘መንፈስ ቅዱስ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍበት የምታየው በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው’ ሲል ነግሮኛል።
እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
ኤፒኮሮሶችና እስቶይኮች የተባሉ ፈላስፎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይከራከሩ ነበር። አንዳንዶቹ “ይህ ለፍላፊ ምን ማለት ይፈልጋል?” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “ስለ አዳዲስ አማልክት የሚናገር ይመስላል” ይሉ ነበር፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስ የኢየሱስንና የትንሣኤውን መልካም ዜና ስላበሠረ ነው።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
ጳውሎስ እዚያ ከነበሩት ሰዎች እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ዐውቆ “ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ከፈሪሳዊ የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ፤ እነሆ! አሁን በፍርድ ፊት የቀረብኩት በተሰጠው ተስፋና በሙታን ትንሣኤ ምክንያት ነው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ በሸንጎው መካከል ተናገረ።
እርግጥ በመካከላቸው ቆሜ ‘የሙታን ትንሣኤ አለ በማለቴ ዛሬ ለፍርድ በፊታችሁ ቀርቤአለሁ’ ብዬ ከፍ ባለ ድምፅ ተናግሬአለሁ፤ ከዚህ በቀር ሌላ ያደረግኹት ነገር የለም።”
ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በተናገረ ጊዜ ፊልክስ ፈርቶ “አሁን ሂድ፤ ሲመቸኝ ሌላ ጊዜ አስጠራሃለሁ” አለው።
ይህም የሚሆነው እኔ በማበሥረው የወንጌል ቃል መሠረት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰዎች በሠሩት ስውር ነገር ላይ በሚፈርድበት ቀን ነው።
አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎች ብንሆን፤ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻ ሰዎችም ብንሆን፥ አንድ ሰውነት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል፤ ሁላችንም ከዚሁ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተናል።
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።
በተጠመቃችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተቀበራችሁ፤ ከእርሱም ጋር ከሞት ተነሥታችኋል፤ ከሞት የተነሣችሁትም ክርስቶስን ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር ኀይል በማመናችሁ ነው።
ሴቶች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን ከሞት ተነሥተው አገኘአቸው። ሌሎችም የበለጠ ትንሣኤ ለማግኘት አስበው ልዩ ልዩ ሥቃይ ተቀበሉ፤ ከእስራት ነጻ መሆንንም አልፈቀዱም።
እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።