ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ዕብራውያን 13:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አምነን፥ “እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በድፍረት፦ ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
እንዲሁም “የአባቴ አምላክ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ በግብጽ ንጉሥም እጅ እንዳልገደል አዳነኝ” በማለት ሁለተኛውን ልጁን ኤሊዔዘር ብሎ ሰይሞት ነበር።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
እስራኤል ሆይ! የእርዳታህ ጋሻ፥ የድልህ ሰይፍ መዳንን ከእግዚአብሔር ያገኘ፥ እንዳንተ ያለ ሕዝብ ከቶ የለም፤ ምንኛ የታደልክ ነህ! ጠላቶች እየተለማመጡ ወደ አንተ ሲመጡ ጀርባቸውን ትረግጣለህ።
እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።
“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”