Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 56:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በእግዚአብሔር ስለምታመን አልፈራም፤ ስለ ሰጠኝም ተስፋ አመሰግነዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ስለምታመን ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነፍ​ሴን ከአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አዳ​ናት። ደን​ግ​ጬም ተኛሁ፤ የሰው ልጆች ጥር​ሳ​ቸው ጦርና ፍላጻ ነው፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም የተ​ሳለ ሾተል ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 56:4
18 Referencias Cruzadas  

ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤


ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ለመጸለይ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ አልፈራም፤ ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?


ቃልህ በጽኑ መሠረት ላይ የተመሠረተ ነው፤ ትክክለኛ ፍርድህም ዘለዓለማዊ ነው።


የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።


ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ እውነተኛነትህ የስምህንና የትእዛዞችህን ከፍተኛነት ስላሳየህ ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እየሰገድኩ ስምህን አመሰግናለሁ።


እግዚአብሔር ብርሃኔና ደኅንነቴ ስለ ሆነ ማንንም አልፈራም እግዚአብሔር የሕይወቴ ከለላ ስለ ሆነ የሚያስፈራኝ ማነው?


ግብጻውያን ሰዎች ናቸው እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ ለባሾች እንጂ የተለዩ መናፍስት አይደሉም፤ እግዚአብሔር በቊጣው በሚነሣበት ጊዜ ይህ የሌሎች ረዳት የሆነው መንግሥት ይደናቀፋል፤ እርሱ ይረዳው የነበረውም መንግሥት ተንኰታኲቶ ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ይጠፋሉ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


እንግዲህ ቅዱስ መጽሐፍን መሻር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ቅዱስ መጽሐፍ አማልክት ብሎ ከጠራቸው


ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።


ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos