ዘፍጥረት 49:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይሳኮር በበጎች መካከል እንደሚተኛ ብርቱ አህያ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይሳኮር፣ በበጎች ጕረኖም መካከል የሚተኛ ዐጥንተ ብርቱ አህያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፥ በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይሳኮር መልካም ነገርን ወደደ፤ በተወራራሾቹም መካከል ያርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው በበጎች ጕረኖም መካከል ያርፋል |
ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።
አቤሜሌክ ከሞተ በኋላ የዶዶ የልጅ ልጅ የፑአ ልጅ ቶላዕ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም ከይሳኮር ነገድ ሲሆን የሚኖረውም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሻሚር ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነበር፤