የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”
ዘፍጥረት 48:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኩትን ለሙን ምድር ሴኬምን፥ ከወንድሞችህ ጋር ከምታገኘው ድርሻ በላይ ለአንተ ብቻ ሰጥቼሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ዐምባ ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ከአሞራውያን በሰይፌና በቀስቴ የወስድሁትን ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ አብልጬ ሰጠሁህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ከአሞራውያን በሰይፌና በቀስቴ የውስድሁትን ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ አብልጬ ሰጠሁህ አለው። |
የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ በርስትነት የምታካፍላቸው የመሬት ድንበር የሚከተለው ነው፤ የዮሴፍ ነገድ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል።
“እኔ ግን ለእናንተ ስል ቁመታቸው እንደ ሊባኖስ ዛፍ፥ ብርታታቸው እንደ ዋርካ ዛፍ የነበረውን አሞራውያንን ከነሥር መሠረታቸው ነቃቅዬ አጠፋሁላችሁ፤
ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።
ስለዚህ ለሕዝቡ ለእስራኤላውያን ሲል አሞራውያንን አባሮ ያስወጣ ራሱ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ፥ አንተ መልሰህ ልትወስድ ታስባለህን?