Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 33:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ድንኳኑን የተከለበትን የሴኬም አባት ከነበረው ከሐሞር ዘሮች ላይ በመቶ ብር ገዛው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ ከኤሞር ልጆች በመቶ ጥሬ ብር ገዛ፤ ኤሞርም የሴኬም አባት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የመስክ ክፍል ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የእርሻውን ክፍል ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 33:19
10 Referencias Cruzadas  

ሁሉም እየሰሙ ዔፍሮንን “እባክህ አድምጠኝ፤ ቦታውን በሙሉ እገዛዋለሁ፤ እነሆ ዋጋውን ተቀበለኝና የሚስቴን አስከሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው።


“ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።”


እዚያም መሠዊያ ሠራና “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።


ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፥ ሲካር ተብላ ወደምትጠራ የሰማርያ ከተማ መጣ።


ዐጽማቸው ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ተቀበረ።


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።


የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos