ዘፍጥረት 47:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በግብጽ አገር ጌሴም በተባለ ምድር ይኖሩ ነበር፤ እዚያም ብዙ ሀብት አገኙ፤ ብዙ ልጆችም ወለዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብጽ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፤ በዚያም ሀብት ንብረት ዐፈሩ፤ ቍጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም በግብጽ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ፥ ገዙአትም፥ ረቡ፥ እጅግም በዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም በግብፅ ምድር በጌሤም ሀገር ተቀመጠ፤ እርስዋም ርስታቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅግም ተባዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በግብፅ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ ገዙአትም ረቡ እጅግም በዙ። |
በዚህ ዐይነት በአገራችን ላይ ከእኛ ጋር መኖር ትችላላችሁ፤ በፈለጋችሁበት ስፍራ በመዘዋወር እየሠራችሁና እየነገዳችሁ ርስትም ይዛችሁ መኖር ትችላላችሁ።”
ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመሄድ አትፍራ፤ እኔ ዘርህን በግብጽ አገር ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ በግብጽ ምድር እንዲቀመጡ አደረገ፤ ፈርዖን ባዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ምርጥ የሆነውን፥ በራምሴ ከተማ አጠገብ ያለውን ቦታ በይዞታ ሰጣቸው።
ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለ ነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ ውስጥ አስገባት።
ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው።
ነገር ግን እስራኤላውያን በተጨቈኑ መጠን ቊጥራቸው ይበልጥ እየበዛና በምድሪቱም ላይ እየተስፋፉ ሄዱ፤ ከዚህም የተነሣ ግብጻውያን እስራኤላውያንን ፈሩአቸው።
የቀድሞ አባቶችህ ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜ ብዛታቸው ሰባ ብቻ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክህ የአንተን ቊጥር ብዛት እንደ ሰማይ ከዋክብት አድርጎታል።
ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምላክህ ፊት ይህን መግለጫ ስጥ፦ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ጥቂት ቤተሰብ ይዞ ወደ ግብጽ በመውረድ መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ ጥቂት የነበረው ታላቅ፥ ኀያል፥ ብዙ ሕዝብ ሆነ።