ዘፍጥረት 32:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሁለት መቶ እንስት ፍየሎች፥ ኻያ ተባዕት ፍየሎች፥ ሁለት መቶ እንስት በጎች፥ ኻያ ተባዕት በጎች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችን፥ ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሃያ የፍየል አውራዎችን፥ ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሃያ የበግ አውራዎችን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችም ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን |
ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።
አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።
በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
በዚያም ቤተሰቡ ከካሌብ ጐሣ የሆነ ናባል ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የማዖን ተወላጅ ሲሆን በቀርሜሎስ ከተማ አጠገብ የእርሻ መሬት ነበረው፤ ታላቅ ባለጸጋ ከመሆኑም የተነሣ ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ ሚስቱ አቢጌልም እጅግ የተዋበች አስተዋይ ሴት ስትሆን እርሱ ግን መልካም ጠባይ የጐደለው ባለጌ ሰው ነበር። ናባል በቀርሜሎስ በጎቹን ያሸልት ነበር፤