Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “እንስሶቹ ለመፅነስ ፍትወት በሚያድርባቸው ወራት የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በመንጋዎቹ መራቢያ ወራት ዐይኖቼን አነሳሁ፥ በሕልምም በበጎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉርና ነቊጣ እንደ ነበሩ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲህም ሆነ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ እነሆም በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችን የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:10
11 Referencias Cruzadas  

በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው።


“ ከመካከልህ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ተነሥቶ ‘ተአምር ወይም አስደናቂ ነገር አደርጋለሁ’ ይል ይሆናል።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤


በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው።


በዱላዎቹ ፊት ለፊት ፍትወት እየተሰማቸው ይጐመዡ ነበር፤ ስለዚህ ሸመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ የሆኑ ግልገሎችን ወለዱ።


በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይወጡና ወደ ታች ይወርዱ ነበር።


እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።


እግዚአብሔር የአባታችሁን የላባን መንጋዎች ወስዶ ለእኔ የሰጠኝ በዚህ ዐይነት ነው።


በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ ‘ያዕቆብ!’ ብሎ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆ፥ አለሁ!’ አልኩ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፤ ላባ የፈጸመብህን በደል ስላየሁ ይህን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤


አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ፤ ሕልሙን ለወንድሞቹ በነገራቸውም ጊዜ ከቀድሞው ይበልጥ ጠሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios