ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዘፍጥረት 28:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፤ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው፥ ባረከውም፥ እንዲህ ብሎም አዘዘው፦ “ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው፤ ባረከውም፥ እንዲህም ብሎ አዘዘው፥ “ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው ባረከውም እንዲህ ብሎም አዘዘው፤ |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ መረቀውና ሚስት እንዲፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደ ላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው፦ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ” ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤
እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፤ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፤ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን።
ከዚህ በኋላ ዮሴፍን እንዲህ ሲል ባረከው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና እኔንም ሕይወቴን ሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ እረኛ ሆኖ የጠበቀኝ አምላክ እነዚህን ልጆች ይባርክ!
እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሙሴ ርስት በባሳን ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለእኩሌቶቹ ደግሞ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ከወንድሞቻቸው ጋር ኢያሱ መሬት ሰጣቸው፤ ኢያሱም ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤