ዘፍጥረት 26:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም በማለዳ ተነሥተው፣ በመካከላቸው መሐላ ፈጸሙ። ይሥሐቅም አሰናበታቸው፤ እነርሱም በሰላም ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማልደውም ተነሡ፥ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ፥ ይስሐቅም አሰናበታቸው፥ ከእርሱም ወጥተው በሰላም ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማልደውም ተነሡ፤ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ፤ ይስሐቅም አሰናበታቸው፤ ከእርሱም በደኅና ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማልደውም ተነሡ እርስ በርሳቸውም ተማማሉ ይስሐቅም አሰናበታቸው ከእርሱም ወጥተው በደኅና ሄዱ። |
“ጌቶቼ ሆይ፥ ተቀብዬ ላስተናግዳችሁ ዝግጁ ነኝ፤ እባካችሁ ወደ ቤቴ ግቡ፤ እግራችሁንም ታጥባችሁ እዚሁ ዕደሩ፤ ጠዋት በማለዳ ተነሥታችሁ ጒዞአችሁን ትቀጥላላችሁ” አላቸው። እነርሱ ግን “አይሆንም፤ እኛ እዚሁ በከተማይቱ አደባባይ እናድራለን” አሉት።
በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።
እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዘሮቼን በማታለል እንዳትበድል እዚህ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤ እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች በመጻተኛነት ለምትኖርባት አገር ታማኝነትን እንደምታሳይ ማልልኝ” አለው።
አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።
ስለዚህ እኔና አንተ በመሐላ የስምምነት ውል እናድርግ፤ ለምናደርገው ውል ምስክር ሆኖ እንዲኖር ድንጋይ ሰብስበን በመከመር ሐውልት እናቁም።”
በዚያን ቀን እስራኤላውያን በራብ ደከሙ፤ ምክንያቱም ሳኦል “ጠላቶቼን እስክበቀል ድረስ ዛሬ እህል ውሃ የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!” ብሎ ሕዝቡን በማስማል ማንም ሰው እህል ውሃ እንዳይቀምስ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሁሉም ምንም ነገር ሳይቀምሱ ቀኑን ሙሉ ዋሉ።
ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።
ዳዊትም “እነዚያ ወራሪዎች ወዳሉበት ስፍራ ልትመራን ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እንደማትገድለኝና ለጌታዬም አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ ከማልክልኝ ላሳይህ እችላለሁ” ሲል መለሰለት።