Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 20:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊት ግን፣ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በነፍስህ እምላለሁ በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም፦ እኔ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፥ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይከፋው አይወቅ ይላል፥ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶአል ብሎ ማለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 20:3
18 Referencias Cruzadas  

ኢታይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታዬ በሚኖርበት ቦታ ሁሉ፥ በሞትም ሆነ በሕይወት እኔ አገልጋይህ በዚያ እንደምገኝ በእግዚአብሔር ስም እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ።”


በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።


ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ኢያሪኮ ሄዱ።


ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ጒዞአቸውን ቀጠሉ።


የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤ የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤ በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።


ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ “እኔ አልገድልህም፤ ለሚገድሉህም ሰዎች አሳልፌ ላልሰጥህ ሕይወትን በሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ!” በማለት በምሥጢር ቃል ገባልኝ።


በእውነትና በቅንነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ ብትምሉ ሕዝቦች ይባረካሉ፤ በዚህም ይመካሉ።”


ሕይወትህ ዘወትር በጭንቀት ላይ ይሆናል፤ የመኖር ዋስትናህም የተረጋገጠ ባለመሆኑ ቀንና ሌሊት በፍርሃት ትዋጣለህ።


አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት አክብረው፤ እርሱን ብቻ አምልክ፤ መሐላህም በእርሱ ስም ብቻ ይሁን።


ሰዎች ሲምሉ ከራሳቸው በሚበልጥ ስም ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ሁሉ ያስወግዳሉ።


ሐናም ዔሊን እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፥ ዕድሜህን ያርዝመውና አንድ ጊዜ እዚህ በፊትህ ቆሜ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይ ያየኸኝ ሴት እኔ ነኝ፤


ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።


ዮናታንም “ይህንንስ ከአንተ ያርቀው! አትሞትም፤ ትልቅም ሆነ ትንሽ አባቴ ከእኔ የሚሰውረው ነገር የለም፤ ይህንንም ነገር ቢሆን አባቴ ከእኔ አይሰውርም በፍጹም አይደረግም!” አለው።


ዮናታንም “አንተ የምትፈልገውን ሁሉ አደርግልሃለሁ” አለው።


የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤


ዳዊት በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “አንድ ቀን ሳኦል እኔን ይገድለኛል፤ እንግዲህ ለእኔ የሚበጀኝ ነገር አምልጬ ወደ ፍልስጥኤም መሄድ ነው፤ ከዚያም በኋላ ሳኦል በእስራኤል ምድር እኔን መፈለጉን ስለሚተው ከእጁ አመልጣለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos