ዘፍጥረት 22:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ‘ብዙ በረከት እንደምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ’ ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቈጠብክ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለው፦ “ጌታ፥ በራሴ እምላለሁ፥ ይላል፤ ምክንያቱም ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልከኝምና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ ለምትወድደው ልጅህም ከእኔ አልራራህምና መባረክን እባርክሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዴህም አለው፦ እግዜአብሔር፦ በራሴማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፦ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምን |
መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው።
እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤
አገልጋዮችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ፤ ዘራቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት ልታበዛውና የተስፋይቱንም ምድር ርስት ለዘለዓለም አድርገህ ልትሰጣቸው በመሐላ የገባህላቸውንም ቃል ኪዳን አስብ።”
ትእዛዜን የማትፈጽሙ ከሆነ ግን ይህ ቤተ መቅደስ ፈራርሶ እንደሚወድቅ በራሴ በመማል አረጋግጥላችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ነገር ግን በግብጽ ስለምትኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ እኔ እግዚአብሔር በኀያሉ ስሜ በመማል የወሰንኩትን ስሙ፤ ከእናንተ ማንም ሰው ‘ሕያው ልዑል እግዚአብሔርን’ ብሎ በስሜ እንዲምል አልፈቅድም።
የቦጽራ ከተማ አስፈሪ ምድረ በዳ ሆና እንደምትቀር እኔ በራሴ ምዬአለሁ፤ ሕዝብ ሁሉ መቀለጃ ያደርጋታል፤ ስሟንም እንደ ርግማን ይቈጥሩታል። በአቅራቢያዋ ያሉ መንደሮች ሁሉ ለዘለዓለም ፍርስራሾች ሆነው ይቀራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የሠራዊት አምላክ በባቢሎን ላይ ብዛቱ እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ሠራዊት እንደሚያመጣባት በስሙ ምሎአል፤ ያም ሠራዊት ድልን በመቀዳጀት ይደነፋል።
“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።