ዘፍጥረት 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም” በማለት ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያኽል ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ታለቅስ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “ልጁ ሲሞት ዐይኔ አያይም” ብላ፣ የቀስት ውርወራ ያህል ርቃ ዐረፍ አለች፤ እርሷም እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ሄደች ብላቴናው ሲሞት አልየው ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ ተቀመጠች። ፊት ለፊትም ተቀመጠች፥ ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሲሞት አላየውም ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ እየተመለከተች፥ ፊት ለፊት ተቀመጠች፤ ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናው ሲሞት አልየው ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ ተቀመጠች። ፊት ለፊትም ተቀመጠች ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች። |
እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ወደ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ያለችኝን ትንሽ ዱቄት ለልጄና ለእኔ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያም በኋላ በራብ ከመሞት አንተርፍም።”
እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤
የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
እያንዳንዳችሁ እንደገና ባል አግብታችሁ ትዳር እንድትመሠርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።” ከዚህ በኋላ ናዖሚ ለመሰናበት ሳመቻቸው፤ እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።