እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።”
ዘፍጥረት 18:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ለእግዚአሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንድ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታግኝለች። |
እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።”
ከሦስቱም እንግዶች አንዱ አብርሃምን “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። እርሱም ይህን በሚናገርበት ጊዜ ሣራ በስተኋላው በድንኳኑ ደጃፍ ቆማ ታዳምጥ ነበር፤
ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርስዋም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው።
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
እዚያም በደረሰ ጊዜ ሐዘን በተሞላበት ድምፅ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ! ዘወትር በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊያድንህ ችሎአልን?” ብሎ ተጣራ።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእኔ የእግዚአብሔር ኀይል ውሱን ነውን? ቃሌ በእናንተ ዘንድ የሚፈጸም ወይም የማይፈጸም መሆኑን አሁን ታያለህ!”
‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።
ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ፦ “እርግጥ ይህ ነገር በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል፤ ለእግዚአብሔር ሁሉ ነገር ይቻለዋል፤” አላቸው።
መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! አትፍራ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ።
እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።
ለእርስዋም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “አንቺ መኻን ነሽ፤ ልጆችም የሉሽም፤ ነገር ግን ትፀንሺአለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤
ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።